የአዲስ አበባ 2019 TVT የሥራ ዓውደ-ርዕይ በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ!

የአዲስ አበባ 2019 TVT የሥራ ዓውደ-ርዕይ በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ!
  • avatar
    Ali Ibrahim
  • Oct 20, 2026

  • 2

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለ15 የቴክኒክና ሙያ (TVT) ኮሌጆች ተመራቂ ሰልጣኞች ያዘጋጀውን ባለ 2-ቀን ታላቅ የሥራ ዓውደ-ርዕይ ከመስከረም 26 - 27 ቀን 2019 ዓ.ም. በስኬት አጠናቋል።

beki.jpg

​ከ100 በላይ ታዋቂ ቀጣሪ ድርጅቶች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይMohas Jobsየዝግጅቱ ይፋዊ አጋር (Official Partner) በመሆን፦

✅ ለ1,600+ ተመራቂ ሰልጣኞች "የሥራ ዝግጁነት እና የማህበራዊ ክህሎቶች" (Job readiness & Soft skills) ስልጠና በመስጠት፤
✅ ቀጣሪ ድርጅቶችን ወደ ዓውደ-ርዕዩ በመጋበዝና በማስተባበር፤
✅ የዝግጅቱን ቅድመ-ተግባራት በማሳለጥና የታቀደለትን ዓላማ እንዲመታ በማድረግ፤
✅ በቀጣሪ ድርጅቶች እና በተመራቂ ሰልጣኞች መካከል ውጤታማ የሥራ ትስስር እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።


photo-2026-10-07-20-40-11.jpg
​ለዚህ ታላቅ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉት ለአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ ለቀጣሪ ድርጅቶች፣ የኮሌጅ አሰልጣኞች እንዲሁም ለተሳተፉ ተመራቂዎች በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን!

​"የነገውን ብሩህ የሥራ ዓለም ጉዞ በጋራ እንጀምር!" 

  • Share post:

Get New Jobs Notification!

Subscribe & get all related jobs notification.